በዕውቀቱ ስዩም
አያቴና ያገሪቱ እርምጃ ሮዝ ነሐሴ 2000 ዓ.ም
አያቴ:-ባገሪቱ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የምግብ እጥረት ዘለቄታዊ መፍትሔ የሚገኝበትን መንገድ ለመቀየስ መኝታ ቤቱን ዘግቶ በምርምር ተጠመደ:: ተመራማሪዎች ነገሮችን የመርሳት ልማድ እንዳላቸው የታወቀ ነው:: . . . አልበርት አንስታይን በምርምር ሲጠመድ ምሳውን ይረሳ ነበር ይባላል:: አያቴ ግን በምርምር ሲጠመድ ምሳ መብላቱን ይረሳና በድጋሚ ያዛል:: በዚህ ምክንያት ከሚመራመርበት ጊዜ ይልቅ ከቀላቢው ጋር የሚጨቃጨቅበት ጊዜ ይበልጥ ነበር:: . . . አልበርት አንስታይን ወደ ሱቅ ገብቶ ዕቃ ገዝቶ ከከፈለ በኇላ ዕቃውን ረስቶ መንገዱን ይቀጥላል:: አያቴ ግን ዕቃ ገዝቶ ክፍያውን ይረሳል:: አንዳንዴ ወጣቶች ወደ እጮኛቸው ቤተሰብ ሽምግልና ይልኩታል:: እሱ ግን ተሸምጋዩ ቤት ሲደርስ ነገሩን ይረሳና ሴቲቱን ለራሱ ይጠይቃል:: . . . አልበርት አንስታይንና አያቴ ተከታይ በማፍራት ረገድም ልዩነት አላቸው:: አልበርት አንስታይን ተከታዮች ነበሩት:: አያቴ ግን ከጥላው በስተቀር ተከታይ አልነበረውም:: የሚያደርገው ምርምር በይበልጥ በእፅዋትና በወፎች ላይ ያተኮረ ነበር:: አንድ ቀን " የባህር ዛፍ ቅጠል ለምግብ አገልግሎት ሊውል እንደሚችል ደርሼበታለሁ! " ብሎ ለፈፈ:: . . . ያገሩ ህዝብ ይህንን ሲሰማ ግልብጥ ብሎ ወደ ቤታችን ተመመ:: አያቴ አንድ ማለዳ ህምህምታ ሰምቶ ቢወጣ አገሬው በረንዳችንን አጥለቅልቆ ተመለከተ:: . . . "የባህር ዛፍ ለምግብ ይውላል ማለትህን ሰምተን ነው የመጣን!" ሲል ጠየቀ የሕዝቡ ተወካይ:: . . . "ልክ ነው !" አለ አያቴ "ግን ባህር ዛፍ ብቻውን አይደለም:: ከትንሽ ጨውና ከትንሽ ስጋ ጋር ጥሩ ምሣ ሊወጣው ይችላል!"

No comments:
Post a Comment