May 20, 2012

የደመወዝ ጭማሪ ቁጥር 1



መምህር ነኝ በሃገራችን ከሚገኙ ዝቅተኛ ትምህርት ተቋማት በአንዱ አስተምራለሁ::ለዚህ ዝቅተኛ የትምህርት ተቋም ኮሌጅ የሚል መጠሪያ ሰጥተውታል::ኮሌጃችን በብዙ መሃይሞችና በጥቂት ልበ ብርሃኖች የሚመራ ጥራቱን የጠበቀ ተቋም ነው::
እንድ ኮለጅ መምህርነቴ በወር ቆጥሬ የማልጨርሰው ደመወዝ በወር ይከፈለኛል::ይህ ብር ብዙ ጊዜ የሚወጣው በወሩ መጨረሻ በመሆኑ ከዛ በሃላ በሚኖረኝ  የገንዘብ መጠን ሳምንታትን እንዲህ ከፍያቸዋለሁ::
ሳምንተ ፍስሃ; ይህ ሳምንተ ደመወዝ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ተከታታይ ሶስት ቀናት ያሉትን ቀናቶች ያካትታል::በነዚህ ቀናቶች ፍስሃ ከእኔ ጋር ትሆናለች:: ባለኝ ብር  ጨከን ብየ አንድ ኮካ ኮላ፣ አንድ ጥብስ እንዲሁም የ 5 ብር የሞባየል ካርድ  በመሙላት ውጭ እን ካሉ ዘመዶቸ ጋር የምገናኝበት ሳምንት ነው::
ሳምንተ ነነዌ: ይህ ሳምንተ በክርስተና ሀይማኖት አማኛች ዘንድ የኣብይ ፆምን መድርስ የሚያመላክት ሳምንት ሲሆን በኔ ወራሂ ኑሮ ደግሞ ለመንፈሳዊ ሳይሆን በችግር ምክንያት የሚመጣ የፆም ወቅትን የሚያመላክት ሳምንት ነው::
ሳምንተ ደብረ ዘይት: ይህ ሳምንተ ደግመ የደሞዝ መምጫ አጋማሽን የሚያሳይ ሳምንተ ነው::
ሳምንተ ህማማት: ይህ ሳምንት ደግሞ ደመወዝ ከመውጣቱ በፋት ያሉትን ቀሪ የመጠረሻ ሳምንተ ቀናትን ታካትታል::በነዚህ ቀናት ችግር ና እኔ ፍቅራችን ይጠነክራል፣ ጥብስ በእይኔ ይዞራል፣እንድሰው ካርድ መሙላትም ያምረኛል::ነገር ግን ሳምንቱ ከፈት የሚጠብቀኝን የፍስሃ ሳምንት በመጠበቅ የምታገሰው  የህማማት ሳምንተ ነው::ፍስሃን ከሩክ እያየሁ በተስፋ እኖራለሁ::ፍስሃን ከሩቅ እያየሁ በተስፋ እኖራለሁ::በፍስሃ ሳምንተ ቀናት ውስጥ ያከናወንቸው ምርጥ ሳምንታዊ ኑሮየ አይኔ ላይ በትዝታ ይመላለሳል::ያኔ የሞላውት የ 5 ብር ካርድ፣ኮካው ናጥብሱም የምባለበት የፍሰሃ ሳምንተ ለመጣ የቀሩት እነዚህ የህማማት ቀናቶች ብቻ ናቸው::
በነዚህ የህማማት ሳምንቶች አናት ውስጥ ሀገራችን ውስጥ  እንደ ፕሪሚየሪሊግ በየአመቱ ከሚከሰተው ተፈጥራዊ ድርቅና ርሃብ ያልተናነሰ ችግር እኔ ቤት ውስጥ ይከሰታል:: በቀን አንዴ ምግብ ማግኝት ዲዚ ሎተሪ ከማሸነፍ ተናነሶ አይታይም::በነዚህ ቀናት ቤቴ ብቻ ሳይሆን ኮሌጁም ያስጠላኛል:: ምክንያቱም መምህሩ ሁሉ ይህን የችግር ወቅት የምሳ ሰኣት የሚያሳልፉት በ ሃይበርኔሽን ዘዴ ነው:: ሀይበርኔኝን አዴ ምሳን ተሽቶ የማሳለፍ ዘዴ ነው::
እንግዲህ ለእኔ የፍስሃ ሳምንት ማነስ ና የህማማት ሳምነት ጊዜ መራዘም ዋነኛ ምክንያት የደሞዝ መጠኔ ነው::እድሜ ለምንግስታችን ለመምህር ልዮ ትኩረት በመስጠት መምህራንን በደሞዝ ሳይሆን በምስጋና እንዲሰራ በማድረግ የመምሀራኑን የማስተማር ፍላጎት ለማነሳሳት ደፋ ቀና ማለት ከጀመረ ዉሎ አድሯል::ከዚህ በተለየ መልኩ ለኛ ዝቅተኛ የትምህርት ተቋም የደሞዝ ማስተካከያ ለማድረግ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ስብሰባ ከጀመረ አመታት አልፎታል::ለነዚህ ጥቃቀን ነገሮች ላይ ትኩረት አድርገው ጥቃቅን ድርጅቶችን ለመደገፍ  ለተቋቋሙ ጥቃቅን ኮሌጆች በጥቃቅን አጥኘወች የተጠና የደሞዝ ጭማሪ ነው::
የኔ ቤት እንደማንኛውም  የመንግስት ቤት የራሱ የሆነ ራእይ ና ተልእኮ አላት
የእኔ ራእይ: በአምስት አመታት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው የሀገራችን ዜጎች እኩል በመሰለፍ በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ ::
ተልእኮየ ደግሞ : ይህንን ራእይ ለማሳካት የደሞዝ ጭማሪ በተስፋ በመጠበቅ በነፃ ማገልገል::
ተስፋ የድሃ ምግብ ነው፣ድሃ በህልሙ ቅቤ ባየጠጣ ምን ይውጠው ነበር ይል ነበር አያቴ::በእርግጥም አሁንስ ተስፋየ ማነው የደሞዝ ጥማሪው አይደለምን::

No comments: