Showing posts with label News. Show all posts
Showing posts with label News. Show all posts

Oct 29, 2013

ሠላይና ተሠላይ፤ ወዳጅና ጠላት

አሜሪካዊ እንደራሴና የሥለላ ጉዳይ አዋቂ ፔተ ሆክስትራን የሚያስደንቀዉ ግን የአሜሪካ ሰላዮች የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥትን ስልክን መጥለፋቸዉ አይደለም።የነፍሬድሪሽ ቁጣና ብስጭት እንጂ።ሆክስትራ እንደሚሉት ካስደነቀ-የሚያስደንቀዉ የጀርመን መሪ ሥልክ መጠለፉን ፍሬድሪሽ የሚመሩት የጀርመን የስለላ ድርጅት አለማወቁ ነዉ።
ARCHIV - US-Präsident Barack Obama und Bundeskanzlerin Angela Merkel unterhalten sich am 18.06.2012 in Los Cabos, Mexiko, beim Familienfoto. Merkel setzt bei der Aufklärung der millionenfachen Datensammlung des Geheimdienstes NSA nun auf eine Reise von Vertretern der Bundesregierung und deutscher Geheimdienste in der nächsten Woche nach Washington. Foto: Peer Grimm dpa (zu dpa Merkel verspricht größtmögliche Offenheit bei US-Ausspähaffäre vom 05.07.2013) +++(c) dpa - Bildfunk+++ ወዳጁ ናቸዉ
ለካሳትሮ፥ ለብሬዥነቭ፥ ለማኦ፥ ለ ደጎል፥ ለንጎ በርግጥ አዲስ አልነበረም።አይደለምም።የኤንርኮ ፔና ኔቶ ኢሜል መጠለፍ- ጉድ አሰኝቶ ነበር።የዲልማ ሮሴፍ-ኢሜል መጠለፍ-አስደንቆ ነበር።የሜርክል ሥልክ መጠለፍስ? ጉዱን ጉድ ዘለቀዉ-እንበል ይሆን።የስላላዉ ቅሌት መነሻ፥ዳራዉ ማጣቃሻ፥ የፖለቲካዉ እድምታዉ መድረሻችን ነዉ-ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።


ሚዚያ ሃያ-አንድ 1943 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ።) ፈረንሳይን ከናዚ ጀርመኖች አገዛዝ ነፃ ለማዉጣት የሚዋጋዉ ጦር አዛዥ ጄኔራል ሻርል ደጎል የነፃዋ ፈረንሳይ ባሕር ሐይል ጦርን ለመጎብኘት ከተጠጉባት ብሪታንያ በብሪታንያ አዉሮፕላን ተሳፈሩ።ቆፍጣናዉ፥ ቁጡዉ፥ እልሐኛዉ ረጅሙ ጄኔራል ከትንሿ አዉሮፕላን እንደተሳፈሩ አብራሪዉ (ፓይለቱ) አዉሮፕላንኗን እንደማስነሳት ትንሽ አንገጫገጨና ወዲዚያዉ አቆማት።ጉዞዉ ተዘረዘ።

አዉሮፕላንኗ ስትፈተሽ የሞተሯ አካል በአሲድ መበላሸቱ ታወቀ።አሲዱን አዉሮፕላንዋ አካል ላይ የረጨዉ ወገን ማንነት-እስካሁን ሚስጥር ነዉ።ጄኔራሉ ግን ያኔዉኑ «የብሪታንያ ሰላዮች ሻጥር» ለማለት አላመነቱም።የአዉሮጳ እብሪተኞች የለኮሱት ጦርነት ዓለምን በሚያነድበት በዚያ ዘመን ወዳጅን ከጠላት መለየቱ-ከባድ ነበር።በዚሕም ሰበብ ደ ጎል እንደጠረጠሩት ብሪታንያዎች አድርገዉት ከነበር-ብዙዎችን ብዙም አላስደነቀም ነበር።
ARCHIV - US-Präsident Barack Obama (r) wischt sich am 19.06.2013 den Schweiß von der Stirn neben Kanzlerin Angela Merkel auf einem Podium vor dem Brandenburger Tor am Pariser Platz in Berlin. Foto: Marcus Brandt/dpa (zu dpa Obama war angeblich in NSA-Abhörattacken gegen Merkel eingeweiht vom 27.10.2013) +++(c) dpa - Bildfunk+++ ተሠላይና አሰላይ


ከብዙ አመታት በሕዋላ የደጎልን ቤተ-መንግሥት የተረኩቡት ፕሬዝዳት ኒኮላ ሳርኮዚ ከጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት ከወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ጋር የነበራቸዉ ግንኙነት ከመሪዎች-ወዳጅነትም ጠንከር፥ ጠለቅ ያለ-ነበር ይባላል።ሳርኮዚ ከሜርክል ጋር ሥላላቸዉ ግንኙነት ሥለሚያደርጉት ዉይይት ሲጠየቁ፥«ሁሌ እንገናኛለን፥ በስልክ፥ እንነጋገር፥ ኤስ ኤም ኤስ እንለዋወጣለንም» እያሉ የግንኙነት ዉይይታቸዉ ደረጃ ዘርዝረዉ ነበር።

የሜርክል መልዕክት ከሳርኮዚ አይን-ጆሮ በሚደርስበት ፍጥነት ከአሜሪካ ሰላዮች ኮምፒዉተር ላይ ይዘረገፍ ነበር።ይሕን በርግጥ ሳርኮዚም፥ ሜርክልም ከኛ እኩል ያወቁት ሰሞኑን ነዉ።NSA በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ የአሜሪካ ብሔራዊ የሥለላ ድርጅት ባልደረባ የነበሩት ቶማስ ድራክ እንደሚሉት ሜርክልን መሠለል ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን መጣስ ነዉ።

«ይሕ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲን ክፉኛ መጣስ ነዉ።ይሕ ለመራሒተ-መንግሥት ሜርክል የግል ጉዳይ ነዉ።የግላቸዉ ተንቀሳቃሽ ሥልክ ነዉ።(ያን መጥለፍ) ለምን አስፈለገ።ከእዉነኛ ጠላትሕ ጋር በምታደርገዉ ዉጊያ የቅርብ ተባባሪሕን?»


ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፥ ዓለም አቀፍ ሕግ በቀዝቃዛዉ ጦርነት ወቅት ነበር።ዛሬም አለ።አንዴም ግን ተከብሮ አያዉቅም።ሕግ፥ ደንብ፥ ሥምምነቱን የሚጥሰዉ ደግሞ ሕግ-ደንቡን ካወጣዉ፥ አስከብረዋለሁ ከሚለዉ ሐያል ዓለም ሌላ ማንም አይደለም።

በቀዝቃዉ ጦርነት ወቅት ልክ እንደ ዓለም አቀፉ ሕግ ደንብ ሁሉ የሞስኮ፥ ቤጂንግ ተባባሪዎች፥ የለንደን-ዋሽግተን፥የቦን ፓሪስ ተሻራኪዎች ጎራ ለይተዉ አንዱ የሌላዉን ሚስጥር ማጭለጉ የፖለቲካዉ ፈሊጥ፥ የስለላዉ ወግ ነበር።

የሐገር መሪዎችን እንቅስቃሴ መከታተል አይደለም መግደል ማስገደልም የፖለቲካ መርሕን የማጠናከር፥ ርዕዮተ-ዓለምን የማዳን-ማስፋፋት ሥልት አካል ነበር።የአሜሪካዉ ማዕከላዊ የሥለላ ድርጅት CIA ሹም ኮሎኔል ጄ ሲ ኪንግ የኩባዉን ኮሚንስታዊ መሪ ፊደል ካስትሮ-ከማስገደል ሌላ ሌላ አመራጭ እንደለሌ የጠቆሙት በ1959 ነበር።

ያኔ ዓለም አቀፍ ማሕበር ዲፕሎማሲ፥ ሕግም ነበር።ዲፕሎማሲ ሕግ፥ ደንቡ የሚረቀቅ፥ የሚወሰን የሚበየነዉ ደግሞ ከኒዮርክ ነበር፥ ከዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ።የአሜሪካዊ ማዕከላዊ የሥለላ ድርጅት CIA ካስትሮን ለማስገደል ስድስት መቶ ሰላሳ-ስምንት ጊዜ ያደረገዉ ወይም አድርጓል የተባለዉ ሙከራ የብዙ መፅሐፍት፥ የዝነኛ ፊልም ርዕሥም ሆኗል።

አያቱላሆች የቴሕራንን ቤተ-መንግሥት ከተቆጣጠሩበት ከ1979 ጀምሮ ኢራን የእስራኤልም፥ የአሜሪካኖችም አሜሪካኖችን የሚመሩት የምዕራቡ ዓለምም ቀንደኛ ጠላት ናት።በሕዝብ የተመረጡት የኢራን ጠቅላይ ሚንስትር መሐመድ ሞስዳቅሕን በ1953 ከስልጣን ያስወገደዉ ማን ነበር? ፓትሪስ ሉምባ እንዴት-እና ማን ገደላቸዉ።ራፋኤል ሊኒዳስ ትሩሔሎስ፥ ንጎ ዲንሕ ዲየምንስ?
US-Bürger demonstrieren am 24.10.2013 nahe dem Kapitol in Washington DC gegen die Überwachung durch Geheimdienste wie die NSA. (Foto: Monika Griebeler / DW) - eingestellt von Andreas Grigo ተቃዉሞ


ጥያቄዉ-ጥያቄ ይወልዳል እንጂ ማብቂያ የለዉም።ዓለምን የሚመራዉ ግን ዓለም አቀፉ ሕግ ዲፕሎማሲ ሳይሆን የሐያላን ፍላጎትና ፍቃድ መሆኑ ሐቅ ነዉ።የሐያላኑን ፍላጎት ለማስከበር ደግሞ በግልፅ የሚታወቀዉ ሐያላኑ ወዳጅ ከሚሉት ጋር መተባበር መሻረክ መወዳጀታቸዉ ነበር።እስከ 2007 ድረስ በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የስለላ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር የነበሩት ፔተ ሆክስትራ እንደሚሉት ግን በስለላዉ ዓለም ከወዳጅም-መሐል ተጠርጣሪ ወዳጅ አለ።

«ይሕ ሊሆን የሚችል ይመስለኛል።በስለላዉ ዓለም ፈረንሳዮች፥ ጀርመኖች፥ እስራኤሎች አሜሪካኖች ሁላችንም ጥሩ ወዳጆች ነን።ግን አንዳችን ሌላችንን የምንሠልልበት ጊዜ ሊኖርም ይችላል-የሚል መግባባት ያለ ይመስለኛል።ይሕ (በሰላዮች ዘንድ) በጣም በጣም የታወቀ ነዉ።»

ኮሚንስቶች የሐቫና፥ የሳንዲያጎ፥ የማናጉዋ የሌሎችንም የደቡብ አሜሪካ ሐገራት አብያተ-መንግሥታትን ሲቆጣጠሩ ወይም ለመቆጣጠር ሲያሰጉ የዩናይትድ ስቴትስዋ የቅርብ ጎረቤት፥ ታማኝ፥ ታዛዥነቷን አጓድላ አታዉቅም።ሜክሲኮ።

ከቀዝቃዛዉ ጦርነት በሕዋላ እነ-ሑጎ ሻቬዝ አሜሪካኖችን የሚቃወም ግንባር ለመፍጠር ሲፍጨረጨሩም ያቺ-የአሜሪካ የቅርብ ጎረቤት በታማኝ ታዛዥነቷ እንደፀናች ነበር።ነዉም።ኤንሪክ ፔና ኒቶ ለፕሬዝዳትነት ሲወዳደሩ-ሲመረጡም እንደ ብዙ ቀዳሚዎቻቸዉ ሁሉ ለሐያል፥ ሐብታም፥ ታላቅ ጎረቤታቸዉ ታማኝ ታዥነታቸዉን እንደጠበቁ ነዉ።

በእጩነት ከተመዘገቡ ጀምሮ በምርጫዉ ካሸነፉ-ለሚንስትርነት የሚሾሙ የሚሽሩትን ፖለቲከኛ ስብዕና ማንነት፥ የሚዘረዝር፥ የምርጫ ዘመቻቸዉን ሥልት የሚያትት መልዕክት ለወዳጅ ተከታዮቻቸዉ ኢሜይል ይፅፋሉ። የNSA ሰላዮች ዋሽግተን ቁጭ ብለዉ የሜክሲኮዉን ፕሬዝዳት ኢሜይል ከፕሬዝዳንቱ ደጋፊ፥ተከታዮች እኩል ያነቡ ነበር።የብራዚሏ ፕሬዝዳት የወይዘሮ ዲልማ ሮሴፍ ኢሜዬልም-እንደዚያዉ ነዉ።

አሜሪካዊዉ ሠላይ ኤድዋርድ ስኖደን ሐገር መስሪያ ቤቱን ክዶ ከኮበለለ ወዲሕ የማይሰማ ጉድ የለም።አንዳድ ዘገቦች እንደሚጠቁሙት የሶቬት ሕብረት ኮሚንስቶች በስታሊን ዘመን የሶቬት ሕብረት ሕዝብ ከሚሠልሉት በላይ የአሜሪካ መንግሥት አሜሪካዉያንን ይሰልላል።ለአሜሪካ ሕዝብ ያልራራ ሥርዓት የፈረንሳይ ኩባንያዮችን፥ የስጳኝ ፖለቲከኞችን፥ የዓለምን ሕዝብ የሜክሲኮ፥ የብራዚል፥ የሌሎች ከሰላሳ በላይ መሪዎችን ቢሰልል-በርግጥ ሊያስደንቅ አይገባም።

ያምሆኖ የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት የሥልክ መልዕክት መጠለፉን ከአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት እስከ ሩሲያ መሪዎች ተቃዉመዋል።የጀርመን ፖለቲከኞች የሜርክል ደጋፊም ሆኑ ተቃዋሚዎችም እኩል አዉግዘዉታል።

«እንደሚመስለኝ ይሕ በጀርመን-አሜሪካኖችን ግንኙነት ያለዉን መተማመን ክፉኛ የሚጎዳ ነዉ።መተማመኑ ዳግም ሊገነባ የሚችለዉ እዉነታዉ በግልፅ ወጥቶ ማየን ከቻልን በኋላ ነዉ።

ይላሉ፥-የዋነኛዉ ተቃዋሚ ፓርቲ የSPD የምክር ቤት እንደራሴዎች አስተባባሪ ቶማስ ኦፐርማን ።ሥለ ጀርመን እና ጀርመንን የሚመለከቱ መረጃዎችን የመሰብሰብ መከታተሉ ሐላፊነት የጀርመን የሥለላ ድርጅት ነዉ።ቡንደስ ናሕሪሽተን ዲንስት።BND በጀርመንኛ ምሕፃሩ። የስለላዉን ድርጅት በበላይነት የሚያስተዳድርና የሚመራዉ ደግሞ የጀርመን ፌደራዊ የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስቴር ነዉ።

የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስትር ሐንስ ፔተር ፍሬድሪሽ ግን የመሪያቸዉን መሰለል እንደማንኛዉም ሰዉ ከመገናኛ ዘዴዎች የሰሙ ያክል ነዉ-የተቆጡት።

«ከአሜሪካኖች ጋር በዚሕ ሁኔታ አንሰራም።መተማመኑ ተበላሽቷል።እና እንደሚመስለኝ የተበላሸዉን መተማመን ለመጠገን ሁነኛ እርምጃ መወሰድ አለበት።»

አሜሪካዊ እንደራሴና የሥለላ ጉዳይ አዋቂ ፔተ ሆክስትራን የሚያስደንቀዉ ግን የአሜሪካ ሰላዮች የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥትን ስልክን መጥለፋቸዉ አይደለም።የነፍሬድሪሽ ቁጣና ብስጭት እንጂ።ሆክስትራ እንደሚሉት ካስደነቀ-የሚያስደንቀዉ የጀርመን መሪ ሥልክ መጠለፉን ፍሬድሪሽ የሚመሩት የጀርመን የስለላ ድርጅት አለማወቁ ነዉ።

«የዋሕነት ይመስለኛል።የጀርመን መንግሥት (ባለሥልጣናት) በወዳጆቻቸዉ ሊሰለሉ እንደሚችሉ ማወቅ ነበረባቸዉ።ነገሩ ከተፈፀመ አስደናቂዉ ነገር የሚመስለኝ፥ (ሥለላዉን) ለማስቆም የጀርመን የስለላ ማሕበረሰብ አስፈላጊዉ አፀፋ-እርምጃ አለመዉሰዱ ነዉ።»


Titel: Demonstration #stopwatchingus gegen NSA und Überwachung in Washington, DC, USA
Schlagworte: NSA, Überwachung, Demonstration, stopwatchingus
Wer hat das Bild gemacht?: Monika Griebeler
Wann wurde das Bild gemacht?: 26.10.2013
Wo wurde das Bild aufgenommen?: Washington, DC, USA ተቃዉሞ
የጀርመንዋ መራሒተ-መንግሥት ስልክ መጠለፉ-መሰላላቸዉም እርግጥ ነዉ።ሜርክል መሰለላቸዉን ፕሬዝዳት ባራክ ኦቦማ ያዉቃሉ-አያዉቁም እያነጋገረ ነዉ።ካወቁ ከመቼ ጀምሮ የሚለዉም ያጠያይቃል። እራሳቸዉ ሜርክል እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳት ፍራንሷ ኦሎንድ የአዉሮጳ ሕብረት ወክለዉ ለኦባማ አቤቱታ ያቀርባሉ። ወደ አንድ ሺሕ የተገመቱ አሜሪካኖች በመንግሥታቸዉ መሠለላቸዉን በአደባባይ ሠልፍ አዉግዘዋል።አቤቱታ፥ ተቃዉሞ፥ ዉግዘት፥ ሰልፉ ምናልባት ይቀጥል ይሆናል፥ መሳለል-መጠላለፉ ያስቆመዋል ባይ ግን የለም።ምክንያት፥-ድሮ እንዲያ ነበር፥ ዛሬ እንዲያ ነዉ።ነገም።በዚሕ ዝግጅት ላይ ያላችሁን አስተያየት ላኩል። ማሕደረ ዜና ቢቃኘዉ ጥሩ ነዉ ብላችሁ የምትገምቱትን ወቅታዊ፥ ብሔራዊ፥ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ በተለመደዉ አድራሻችን ጠቁሙን።ለዛሬዉ ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰመን።

Oct 27, 2013

ኢትዬጲያ ቡና ከ ቲፒ ማዚምቤ በአዲስ አበባ…—600 ታዋቂ ሰዎች ይመጣሉ!


ሞ ኢብራሂም የተባለዉ ልጥጥ ሀብታም በየአመቱ የአፍሪካ ጥሩ ሰሪ መሪዎችን በመሸለም ይታወቃል፤ሞ ፋዉንዴሽን የተባለዉ የእርዳታ ድርጅቱ ከዚህ በፊት እንደ ማንዴላ እና መሰል መሪዎችን በመሸለም ይታወቃል፤ለምሳሌ አንዴ የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ መሪ ተብሎ የተመረጠ ሰዉ 5ሚልየን ዶላር ብር ስጦታ ከዛም በየአመቱ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ 200ሺ ዶላር ይበረክትለታል፤ዘንድሮ ከ48ት የአፍሪካ ሀገራት ለዚህ የሚመጥን ሰዉ አልተገኘም፤ነገር ግን ፕሮግራሙ ያለ ተመራጭ መሪ በሙዚቃ ሰዎች በእግር ኳስ ዉድድር ይካሄዳል፤600 ታዋቂ ሰዎች..መሪዎች እና የሙዚቃ ባለሙያዎች ይገኛሉ፤የሙዚቃ ዝግጅትም ይኖራል፤ገቢዉ ለባለሜዳዉ ቡድን ቡና ይሆናል፤
ይሄ ቱጃር ከ15ቀናት በሁዋላ በአዲስ አባ ስታድየም ኢትዮጲያ ቡና እና ቲፒ ማዚምቤን ያጫዉታል፤የአፍሪካ ህብረት መዲና ስለሆነች አዲስ አበባ ለዚህ ጨዋታ ቦታነት ስትታጭ ብዙ ደጋፊ ያለዉ ክለብ በሚል ኢትዮጲያ ቡና በዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ተመርጥዋል፤ዉድድሩ ጥቅምት 29 ይደረጋል፤ቲፒ ማዚምቤ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫን ወስድዋል፤ዘንድሮ ደግሞ በኮንፌዴሬሽኑ የፍጻሜ ተፋላሚ ነዉ፤
የሁለቱን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ኢትዮያዉያን ናቸዉ፤በነገራችን ላይ ተፒ ማዚምቤዎች ኢትዮጲያዊዉን ዳኛ ዘካርያስን በሴካፋ ክለቦች ጨዋታ መተዉታል፤ሜዳዉ ዉስጥ ሮጦ አመለጣቸዉ እንጂ ብዙ ለካልቾና ለቡጢ የተዘጋጁ ተጫዋቾች ነበሩ፤ይህ የሆነዉ ከ2 አመት በፊት ነዉ፤የነሱ አሰልጣኝ የነበረዉ ዲዮጎ ጋርዚያቶ ነበር፤መቸስ ዘካርያስ እንዳያጫዉተን አይሉም….እሱስ ምን ያስብ ይሆን በሜዳዉ ሲያያቸዉ???

በኢትዮጵያ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ የቆየ ማንዴላን የተመለከተ የደህንነት ሚስጥር ይፋ ሆነ

በኢትዮጵያ ከግማሽ ክ/ዘመን በላይ የቆየ ማንዴላን የተመለከተ የደህንነት ሚስጥር ይፋ ሆነ።ሚስጥሩን ማንዴላም እስካሁን ድረስ አይውቁትም።
የማንዴላ አሰልጣኝ ጄኔራል ታደሰ እና ኔልሰን ማንዴላ ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረ-አፓርታይድ (የዘር-መድሎ) ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል።ለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1962 ዓም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በወቅቱ ለማንዴላ ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች።

ከዘመናት በኃላ ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት የግድያ ሙከራ ተደርጎ እንደነበር ሚስጥሩን ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ይዘው የቆዩ በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ፖሊስ መኮንን ዛሬ ጥቅምት 15/2006 ዓም ለመጀመርያ ጊዜ በሸገር ራድዮ የዜና እወጃ ላይ ገልፀዋል። ሻምበል ጉታ ዲንቃ በንጉሡ ዘመን የፖሊስ መኮንን ነበሩ። ማንዴላን በከፍተኛ ሚስጥር እንዲጠብቁ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ጄኔራል ታደሰ(የማንዴላ አሰልጣኝ በወቅቱ ኮ/ል የነበሩ)፣ኮ/ል ፍቃደ እና ሻምበል ፈቃደ ውስጥ ነበሩ።ዛሬ የ76 አምቱ የእድሜ ባለፀጋ ሻምበል ጉታ ዲንቃ ለሸገር ሲናገሩ እንዲህ አሉ። '' ማንዴላን እንድጠብቅ ኃላፊነት የተሰጠኝ እኔ ነበርኩ።ማንዴላ የሚያድሩበት እና ወታደራዊ ስልጠና የሚወስዱበት የኮልፌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ቦታ በተለይ እርሳቸው የሚገኙበት ቦታ 'የፈንጅ ወረዳ' ነበር የሚባለው።ከአራታችን በቀር ማንም ወደ እርሳቸው ቦታ ዝር ማለት አይችልም። ሲተኙ መስኮት ከፍተው ነው የሚተኙት።አንድ ቀን ታድያ አብሮኝ ከሚሰራው የፖሊስ ባልደረባዬ በጥብቅ እንደሚፈልገኝ ነገረኝ።ጣይቱ ሆቴል ተቀ...ጣጠርን እና ሃሳቡን ገለፀልኝ።'' ካሉ በኃላ አሁን አዲስ አበባ ላፍቶ አካባቢ ነዋሪ የሆኑት ሻምበል ጉታ በመቀጠል እንዲህ ብለዋል- ''ጣይቱ ሆቴል የወሰደኝ ሰው ለጊዜው 2000 ፓውንድ በወቅቱ አስቡት 2000 ፓውንድን እና ሰጥቶ እንዲህ አለኝ- 'ሁለት ዕድል ከፊታችን ተቀምጧል።ሊያመልጠን አይገባም።ከፍተኛ ገንዘብ እናገኛለን።ቀጥሎም ወደ ውጭ ሀገር የመሄድ ዕድል አለን።ከአንተ የሚጠበቀው ማንዴላ በተኛበት ዛሬ ሌሊት በመስኮት ገብተህ በገመድ አንቀህ ግደል እና ውጣ እንደወጣህ መኪና ተዘጋጅቶ ይጠብቅሃል ከእዚህ

የውትድርና ሕይወት እንገላገላለን' አለኝ። እኔም ጉዳዩን ከሰማሁ በኃላ በጉዳዩ የተስማማሁ መስዬ ቀጥታ ለጀኔራል ታደሰ ነገርኩኝ። ጉዳዩ በሚስጥር ተይዞ ይህንን ያደረጉት ሰዎች ተደረሰባቸው እና ከሀገር እንዲወጡ(እንዲባረሩ) ተደረጉ ይህ ሚስጥር ለዘመናት ከእኔ ጋር የኖረ ነው።ጉዳዩን ማንዴላም አያውቁትም።'' ብለዋል። Image ኢትዮጵያ ለኔልሰን ማንዴላ የሰጠቻቸው ፓስፖርት ኔልሰን ማንዴላ በወቅቱ እንደ ሻምበል ጉታ ዲንቃ አይነት ታማኝ የኢትዮጵያ የፖሊስ መኮንን ባይገጥማቸው ኖሮ የደቡብ አፍሪካ የነፃነት ታሪክ ሂደትም ሆነ የነፃነት ትግሉ ታሪክ ሌላ መልክ በያዘ ነበር።ይህ ጉዳይ እጅግ ትልቅ ጉዳይ ነው።የኢትዮጵያ ፖሊስ ለአፍሪካ ያደረገው አስተዋፆ የሚያጎላ፣ኢትዮጵያ ለደቡብ አፍሪክ ያደረገችው ትልቅ አስተዋፆ በመሆኑ በኢትዮጵያ የዜና አገልግሎቶች ሁሉ ትኩረት ተሰጥቶት የዓለም አቀፍ የዜና ሽፋን እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ ለኢትዮጵያ ፋይዳው ብዙ ይመስለኛል። በመሆኑም ቢያንስ ለሻምበል ጉታ ዲንቃ የኢትዮጵያ ፖሊስ ጠርቶ ከማዕረግ እስከ ሽልማት ከእዚህ ባለፈም ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት እና ማንዴላ በሕይወት ዘመናቸው ሳሉ ሻምበል ጉታ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ሄደው እንዲያገኙዋቸው ማድረግን ሁሉ ይጠይቃል።ጉዳዩ የደህንነት ሚስጥር የነበረ በመሆኑ በወቅቱ ግድያውን ሊፈፅም የሞከረው አካል ወይንም ሀገር (ማንነቱን ሻምበል ጉታ አልገለፁም (የተባረሩት ዜጎች የየት ሀገር እንደነበሩ አልገለፁም) ዛሬ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለሚኖረው ግንኙነት ጥላ እንዳያጠላ ስጋት ስለሚሆን ዜናው በተፈለገው ደረጃ ለዓለም ሕዝብ እንዳይደርስ የሚደረጉ ስውር ስራዎች እንደማይጠፋ ማጤን ሌላው ሥራ ሊሆን ይችላል። ማንዴላ ከእስር እስኪፈቱ ድረስ በኢትዮጵያ ፓስፖርት ነበሩ።ይህ የደቡብ አፍሪካ ፓስፖርት ከእስር በተፈቱ በ 8ኛ ቀን ያገኙት ነው።

“ለዋልያዉ ልጫወት”…በቻምፕዮንስ ሊግ የተጫወተዉ ዋሊድ አታ


ይህ ከዋሊድ አታ የስዊድኑ ሂልስነቦርግ ተከላካይ ለTeam Ethiopia የfacebook pageየተላከ ደብዳቤ ነዉ፤ተጫዋቹ በዩሮፓ ሊግ እና ቻምፕዮንስ ሊግ ተጫዉትዋል፤ለዋልያዉም ለመጫወት ፍላጎቱን የገለፀዉ ከናይጄሪያ ጨዋታ በፊት ቢሆንም ከዋልያ በኩል ምንም ምላሽ አላገኘም..ከዚህ ደብዳቤ ጋር አብሮ የተጫዋቹን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ምስል አለ..እናም እናንት የዋሊድን ጥያቄና ምስሉን አይታችሁ ትፈርዱ ዘንድ እነሆ!!!
My name is Walid Atta, born in Riyadh in Saudi Arabia in August 28th 1986. My career as a professional football player started in early 2008 when I joined team AIK in Stockholm Sweden. Team AIK was founded in 1891 (122 years ago) and is measured as top club in the Swedish league for decades. During my engagement with AIK (3 years) I gained a lot of experience in all aspect of professionalism as a football player. Throughout these years a became a key player and performed very well in many games in the league also in some international games as well. These 3 successful years became my key to the Swedish national team of U21 and many offer from international clubs, like Glasgow Rangers from Scotland, Valencienne from France and Dinamo Zagreb from Croatia and a few more. After consulting family and my agent I decided to sign up for Dinamo Zagreb from Croatia. Less successful journey with injuries and unstable club economy leading to the club not been able to pay players’ salaries.  Subsequently free ticket from Dinamo Zagreb to leave the club and sin up for any other club with no obligation what so ever.

Helsingborg IF, Swedish football clublocated in a city of  Helsingborg. the club was previous year champions of Swedish league which means Europa Champions League qualifications games to be played if I signed up for the club which I did. Successful story again many international games like hanover 96, Levante and Twente , 7 goals as a center back more than any defender in the league, many offers from clubs in Europe, and voted to be player of the year.

I  have been following the Ethiopian national team in African cup and world cup qualification and I am so impressed and proud how they are progressing just getting better and better It looks good and promising for Ethiopian football in future and hopefully I can be a part of that team and contribute to an even greater success, that would be a fantastic honor.

Kind Regards
Walid Atta

የኢትዮጲያ እግር ኳስ: በስሜትና በእዉነት መካከል!


“ከታሪክ መማር የማይፈልግ ሰዉ ታሪካዊ ስህተትን ለመድገም የተረገመ ነዉ”
በሰኢድ ኪያር
እንደመግቢያ
አሁን ሰማይ የተሰቀሉ ስሜቶች ቀዝቅዘዋል፤በጭፍን ዋልያዉን ከማሞገስና ከመስቀል በእዉነታዎች ላይ መወያየት ተጀምርዋል፤በመጀመሪያዉ ጎን ደግሞ ናይጄሪያን በመልስ ጨዋታ ስለማሸነፍ መዘመሩን ቀጥልዋል፤ይህ ሚድያዉን ያጠቃለለ ፉከራ ከጥቅምት 3ቱ በጥቂት ግን ወሳኝ ነገር ለየት ይላል፤ቢያንስ ቢያንስ ”እንዴት???” የሚለዉን ቀም ነገር ማካተት ጀምረዋል፤ይህ ጽሁፍም ያልተስተዋለዉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስሜት ዝብርቅርቅ ይዳስሳል..ከእዉነት ይልቅ ስሜትን ስለተከተሉት ወቅቶች………
የዛን ቀን ደስታ ልዩ ነበር፤ከዳሪሰላም ታንዛኒያ ሲቃ የተሞላባቸዉ ድምጾች የኢትዮጲያን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ አበሰሩ፤ለእግር ኳሱ ትንሳኤ ቀን እንደሆነም በመነገሩ አዲስ አበባ እና መላ ኢትዮጲያም ተነቃንቀዋል፤በለንደን ኦሎምፒክ ወንዶቹ ሲያቅታቸዉ እንስቶቹ ግን የተለመደዉን ወርቅ አምጥተዉ ህዝቡን አኩርተዋል፤እናም በእግር ኳሱ የዉጤት ማማ ሴቶች ነገሱበት፤”የሴቶች እግር ኳሱ መነቀቃት”ም በይፋ ተነገረ!!በየመንገዱ ሉሲ– በየራድዮ ጣቢያዉ- ጋዜጦች እና የቲቪ መስኮቶች የሉሲ ገድል ዝማሬ ጣሪያዉን ነካ፤ሉሲዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸዉ ይበል የሚያሰኝ ነገር ነዉ፤እንዴት አለፉ የሚለዉ ግን በሞራልና በጮቤ ረገጣዉ መሀል ተሸሽገዉ ቦታ አላገኙም፤ሁሉም ቀርቶ ሉሲዎቹ ከዚህ በፊት ለአፍሪካ ዋንጫ ባለፉባቸዉ ዉድድሮች እንኩዋን ምን ገጠማቸዉ የሚለዉን ማየት አልተቻለም፤አላማችን ለአለም ዋንጫ ማለፍ ነዉ—ስሜት የነገሰበት የሁሉም የርእይ ስንቅ ነበር፤ ዉድድሩ ሲጀመር ግን ይህ ሁላ የስሜት ሰቀላ ዉሀ ተቸለሰበት፤ከመጀመሪያዉ ደቂቃ አንስቶ ኮትዲቫሮች ግብ ማምረት ጀመሩ፤5-0 ጨዋታዉ አለቀ፤እዚህ ላይ ቡድኑ ልምድ የለዉም እንዳይባል 3ተኛ የአፍሪካ ዋንጫቸዉን የሚጫወቱ–ለ2ተኛ ጊዜ ሉሲን በአህጉሪቱ መድረክ የሚወክሉ…በተለያዩ ማጣሪያዎች ልምድ ያላቸዉ ተጫዋቾች የተሰባሰቡበት ቡድን ነዉ፤ግን አልቻለም፤ያቃተዉ ደግሞ የኮትዲቫሮችን ማጥቃት ማቆም ብቻ አይደለም መሀል ሜዳዉን አልፎ መሄድ የዳገት ያህል ለሉሲዎቹ ከበደ፤ናይጄሪያ ቀጣዩን ጨዋታ 3-0 ረታች፤ከካሜሩን ጋር 0-0 የሉሲዎቹ መጨረሻ ከ8ቱ ቡድኖች 8ተኛ ..ብዙ ግቦች ያስተናገዱ ግን አስደንጋጭ ሙከራ እንኳን ያላደረጉ ሁነዉ ተሸኙ፤ከምንም በላይ ‘’ተነቃቃ’’ የተባለዉ እግር ኳስ አሸለበ፤የያኔዉ አይነት ጎሮ ሸባዮ አሁን በሉሲዎቹ አከባቢ የለም፤አርቴፊሻሉ መነቃቃት በክለቦች የዋንጫ ጨዋታ እንኳን አይኖችን መግዛት አልቻለም፤”ብዙ ትምህርት አግኝተንበታል “–የተለመደዉ ሽንፈት ሰራሽ መልስ ተከተለ፤ ይህ ከሆነ 1 ድፍን አመት ሁኖታል፤ስለ ሉሲ ያኔ የተዘመረዉን ያህል አሁን ስለ ሉሲ የሚያወራም የለም፤እንደእምቧይ ካብ በሚናዱ የስሜት ዝብርቅርቆች መሀል ከተገኙት የኢትዮ ቡድኖች አንዱ ሆኑ ..ሉሲዎች ዋልያ…. ከኢትዮጲያና ሱዳን ጨዋታ በፊት–ግዮን ሆቴል –“የኢትዮጲያ እግር ኳስ እንዴት ከወደቀበት እናንሳ?’’ በሚል ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ፤ፌዴሬሽኑ ነዉ የጥናት ባለቤቱ..እናም ከትምህርት ተቋማት የተዉጣጡ ዶክተሮችም ሳይቀሩ ተሳትፈዉበታል፤ማጠቃለያዉ –የኢትዮጲያ ኳስ እንዲያድግ መሰራት የሚገባቸዉ ነገሮች ተብለዉ…. –አደረጃጀትን ዘመናዊ ማድረግ —-ፕሮጀክት በስፋት እንዲኖሩ –ወጥ ስልጠና ማንዋል ማዘጋጀት —አካል ብቃት ላይ በሚገባ መስራት..ወዘተ…. በሚል ጥናቱ አስቀመጠ፤ለዚህም ተሰብሳቢዉ ማረጋገጫ ቃሉን ሰጥቶ ተለያየ፤ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮች ለመፍታት ቢያንስ ቢያንስ አመታት ይፈጃሉ፤አጥኚዎቹም ሆኑ ተሳታፊዎቹ ይህንን ነገር አላምጠዉ ሣይጨርሱ ዋልያዉ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈ፤እዚህ ላይ ሁነኛ መነጋገሪያዎች መነሳት ይገባቸዉ ነበር፤ወይ ጥናቱ ፉርሽ ነዉ!! አልያም ጥናቱ ትክከል ሆኖ ቡድኑ በአጋጣሚ አለፈ፤ካልሆነም ደግሞ ጥናቱ እንደችግር ያስቀመጣቸዉ ሀሳቦች እንዳሉ ሆነዉ ጠንካራ ለአፍሪካ ዋንጫ የሚያልፍ ቡድን ሊሰራ ይችላል….!!.ስሜት መር የሆነዉ እግር ኳሱ ግን ጆሮ ዳባ ብሎ ጉዞዉን ቀጠለ! ቤኒን ጋር አቻ..ሱዳንም ጋር አቻ ወጥቶ ዋልያዉ ደቡብ አፍሪካ ደረሰ፤ይህ በርግጥም ከታሪክ አንጻር ትልቅ አጋጣሚ ነዉ፤ግን ከስሜት ምህዋር ያልወጣ ያለጊዜዉ የደረሰ አልያም የማይደገም ስለመሆኑ ማሳያዉ በዉድድሩ ላይ የታየዉ ቡድን ነበር፤”ዋንጫ እንደርሳለን—ባይሆን እንኳን 4ቱ ዉስጥ ከገባን በቂያችን ነዉ!!”የሚል እቅድም ተነድፎ ነበር፤ ከዛምቢያ ጋር አቻ የወጣዉ ቡድን ሜዳ ላይ ባሉ መነጻጸሪያዎች ሁሉ(ካርድንም ሳይጨምር) ተበልጥዋል፤በስሜት በሚነጉደዉ እይታ ግን ይህ ቡድን የአፍሪካ ባርሴሎና ተባለ፤ቀጠለና በቡርኪና ፋሶ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ እናም 4ት ግቦች አስተናገደ፤በስሜት የተወጠሩት ልቦች አሁን ተንፈስ አሉ፤ናይጄሪያም ብልጫዉን ወስዶ 2-0 አሸነፈ፤ከተሳታፊ ቡድኖች በአነስተኛ ነጥብ በአነስተኛ ሙከራ እናም በብዙ ግቦች በማስተናገድ ግምባር ቀደም ሁኖም ተመለሰ፤”እንደጀማሪ የነጻ ትግል ተፋላሚ”!!! ይህ ነገር በዚህ ትዉልድ ብቻ የተከሰተ አይደለም፤እግር ኳሱ— ከዚህ በፊት የነበሩት ቡድኖች አንዴ ብልጭ ካዛም ድርግም በሚሉ ዉጤቶች ተጭበርብሮ በግድ የኢትዮጲያን እግር ኳስ ትንሳኤ መስክሯል፤
አዘናጊዎቹ ድሎች
3ተኛዉ የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጲያ ትልቁ ታሪክ ነዉ፤ሉቻኖ ቫሳሎ ከንጉሱ እጅ ታሪካዊዉን የአፍሪካ ዋንጫ ከተቀበለ ወዲህ ማንም ኢትዮጲያዊ ያንን መድገም አልቻለም፤ይሔ ድል ለያኔዉ ትዉልድ ብቻ ሳይሆን” ኳስ ድሮ ቀረ” ለሚለዉ መካካለኛዉ የእግር ኳስ ዘመን ሰዎችም እንደማሳያ ይቆጠራል፤የያኔዉ ድል እንዴት ተገኘ?የሚለዉን ዋነኛ ነገር ያልመረመረዉ ትዉልድ ለተከታታይ ዉድቀቶቹ ምክንያት እስኪያጣ ድረስ ግራ ተጋብትዋል፤አስኪ ዋንጫ የበላ ቡድን እንዲህ አይነት የሽንፈት ጉዞ ሲከተለዉ ምን ይባላል፤—ዉጤት ያመጣበትን ምክንያት አለማወቁ ከማለት ዉጭ!!!ተከታዩ ዉጤት ታሪካዊዉ ድል አድራጊ የኢትዮጲያ ቡድን የአፍሪካን ዋንጫ ካነሳ በሁዋላ ባሉት አመታት ያስመዘገባቸዉ ዉጤቶች ናቸዉ!! ከ4ተኛዉ እስከ 13ተኛዉ የሊቢያ አፍሪካ ዋንጫ 6ት ዉድድሮችን ተካፍሎ..ካደረጋቸዉ 19 ጨዋታዎች 14ቱን በሽንፈት 1ዱን አቻ 4ቱን በማሸነፍ አጠናቅዋል፤41 ግቦች አስተናግዶዋል 20 ብቻ አስቖጠወርዋል..21 እዳ ማለት ነዉ ሲወራረድ፤ያስከበረዉ የበላይነት አልያም ያስጠበቀዉ ክብርም አልነበረም፤ጭራሽኑ ከ13ተኛዉ በሁዋላ 31 አመታት እልም ብሎ ጠፍትዋል፤መነቃቃትን ፈጥሮ የነበረዉ ቡድን የተከተለዉ ታሪክ እንግዲህ ይህ ነዉ!!!! ነገርየዉ ይቀጥላል፤የሲካፋ ዋንጫ በኢትዮጲያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ ኢትዮጵያ ዋንጫ አነሳች..ጎሮ ወሸባዉ ቀልጦ በቀጣይ ሽንፈቶች ደግሞ እንደበረዶ መቅለጥ ተከትለዋል፤የክለቦችም ወግ ቢሆን ከዚህ እላፊ አልሄደም፤ አለም ዋንጫ… “ አርጀንቲና አትሄዱም”….. “አርጀንቲና አትሄዱም”…. የሚሉ የተስፋ መቁረጥ ድምጾች በአዲስ አበባ ስታድየም የተሰሙት በጋርዚያቶ ተመርቶ ለአለም ዋንጫ ባለፈዉ የወጣት ቡድን ላይ ነበር፤በህዝብ እና በካፍ ቀና እርዳታ ወደ አለም ዋንጫዉ ማለፉን ያረጋገጠዉ ወጣት ቡድን በጥሎ ማለፋ በአንጎላ 5-2 በደረጃ ጨዋታ በግብጽ 2-0 በጨዋታ ብልጫ ጭምር ሲሸነፍ ህዝቡ ወደ አለም ዋንጫ የማለፍ ትርጉም አልባ መሆኑን በማሰብ ነዉ.አርጀንቲና አትሄዱም ያለዉ!! አሁን ከ13 አመታት በሁዋላ የያኔዉን ለአለም ዋንጫ ያለፈ ቡድን ስናየዉ በርግጥም ተመልካቹ ትክክል እንደነበር ማረጋገጥ እንችላለን፤ቡድኑ እንደምንም ማጣሪያዉን አልፎ(ከ5ጨዋታ 1ዱን በልዩ ህግ አሸንፎ) በአለም ዋንጫዉ በታናናሾቹ 3ቱንም ጨዋታ ተሸንፎ ተመለሰ፤(ከ8 አንድ አሸንፎ ማለት ነዉ)!ወጣት የተባሉቱ በዋናዉ ቡድን ይህንን መድገም አልቻሉም፤ጭራሽም ለረጅም አመታት ለመጫወት የበቁት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸዉ፤ እዚህ ላይ ዋናዉ ነገር ተጫዋቾቹ ያገኙትን ድል ማንኳሰስ አይደለም፤ለሁሉም ኢትዮጲያን በአለም ዋንጫ ለወከሉ..ማጣሪያዉን ለተጫወቱ..ላሰለጠኑ ላገዙ—ለሁሉም ትልቅ ክብርና ምስጋና ሊቸር ይገባል፤ዋናዉ ቁም ነገር ግን የያኔዉ ድክመት ለዛሬዉ ማስተማሪያ ስለሚሆን ዋነኛ ድክቶቹን ነቅሶ ማዉጣት ነዉ፤እናም ኢትዮጲያ ዛሬ ላይ ሁና የዛሬ 13 አመት ለአለም ዋንጫ ያለፈዉ ቡድንዋ ምን እንደጠቀማት መናገር አለመቻልዋ ነዉ! አለም ዋንጫን ማለፍ ሁነኛ ጥቅም ከሌለዉ የወራት ሆይ ሆይ ሆይታ እናም ቀጥሎ ሀዘን የሚያስከትል ከሆነ ዋጋ ቢስነቱ ያይላል!!በተደጋጋሚ የመሳተፍ የሚያስችል ቁመና ያለዉ ጠንካራ ቡድን ከሆነ በሴካፋ ዉድድርም ቢሆን ጥንካሬዉ ሲገነባ ለነገ ተስፋ ይሠጣል፤
የአሁኑ ዋልያ…
የላይኛዎቹ መነሻዎች አሁን ካለዉ ቡድን ጋር ለማያያዝ ጠቃሚ ይሆናሉ፤የዋልያዉ የአፍሪካ ዋንጫ ሂደት ሲገመገም ከማለፍ በስተቀር በዉድድሩ ላይ ያሳየዉ ነገር ጠንካራ እንዳልሆነ ምስክር አያስፈልገዉም፤ከዛ በሁዋላ ባደረጋቸዉ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎችም ቦትስዋናን እና ሴንትራል አፍሪካን በደርሶ መልስ ደቡብ አፍሪካን አዲስ አበባ ላይ ማሸነፍ ቢችልም ጨዋታዎቹ ለቡድኑ ጥንካሬ ምስክር መሆን አልቻሉም፤አዲስ አበባም ላይ ሆኑ ዉጭ የተደረጉቱ ጨዋታዎች አስጨናቂ ነበሩ፤የጨዋታዎቹ ፍጻሜ ፊሽካ እስኪነፋ ድረስ ደረትን ነፍቶ የቡድኑ ጠንካራ ነገር ይህ ነዉ ለማለት አዳጋች ነበር፤የተጋጣሚዎች መቅለል–ማለትም እንደከዚህ ቀደሞቹ ቡድኖች አይነት የነ ግብጽ-ካሜሮን–ቱኒዚያ አይነት ጠንካራ ቡድኖች ጋር አለመጫወቱ–እንዲሁም በዉጤት ደረጃ ጥሩ ባይሆንም በማሸነፍ እድለኛነት እዚህ ደርስዋል ቀደም ብለን እንዳየናቸዉ ቡድኖች አንዴ ታይቶ ብን ብሎ የሚጠፋ ክስተት እንዳይሆን አሁን ላይ ያሉትን ህጸጾች ነቅሶ ማዉጣት ግድ ይላል፤ዋልያዉ የዛሬ 2ት አመት ከተሳተፈበት ሴካፋ ጀምሮ ተጋጣሚን እንዴት እንደሚቀርብ ለማወቅ ከባድ ነዉ፤በአብዛኛዉ ከአሰልጣኞቹ እንደሚሰማዉም..ተጋጣሚ ከተከላከለ የሚያጠቃ— ካጠቃ ደግሞ የሚከላከል ስለመሆኑ ነዉ፤ይህ ነገር ማሸነፍን እንዴት እንደሚመጣ አልያም ሽንፈት በምን ምክንያት እንደመጣ የሚያስተምር አይደለም፤ቄሱም መጽሀፉም ዝም ብሎ ከመቀጠል ዉጭ! የአሁኑ ዋልያ አጨዋወት ግምት ላይ የተመሰረተ ረጅም ኳሶችን አዘዉታሪ መሆኑ በጨዋታዎች ላይ ተመልክተናል፤ይህ ደግሞ አሁን አለም እየተቀየረበት ካለዉ አጨዋወት በሚልየን ምይሎች ርቀት ላይ ያስቀምጠዋል፤ተከላካዮች ኳስን ተጫዉቶ ከመዉጣት ይልቅ በረጅሙ ጠልዞ እንደገና የመጠቂያ ምንጭ እንደሆኑ በተደጋጋሚ አይተናል፤አማካዩ ክፍል ለፈጠራ ዝግ ነዉ፤አለም ትቶት የወጣዉን በተከላካይ አማካዮችን አብዝቶ ያለጨዋታ አቀጣጣይ አነስተኛ ፈጠራ ያላቸዉን ተጫዋቾች መጠቀም የአሁኑን ዋልያ መሀል ሜዳ እጅጉን ደካማ ያደርገዋል፤3ት ቅብብል ለማድረግ የሚቸገር አማካይ ክፍል በንጽጽር ጥሩ ለሚባሉት አጥቂዎች የሚያበረክተዉ አስተዋጽኦ ኢምንት ነዉ፤በዚህ ቦታ በተደጋጋሚ የአሰልጣኞች ምርጫ ያልነበረዉ ሽመልስ በቀለ ለብቻዉ ኢትዮጲያ ምን አይነት ተጫዋቾች እንደሚያስፈልጋት የሚያሳይ ሁኑዋል፤ እነዚህና እና መሰረታዊ የሚባሉ የቡድን ዉህደት ችግር ያለበት ዋልያ ከምንም በላይ አቆለጳጵሶ፤ከአቅሙ በላይ አወድሶ፤የህዝብን ስሜት አንሮ በስተመጨረሻ አሸማቃቂ አይነት ብልጫ ሲመጣ ምክንያት መደርደር ብልህነት አይሆንም፤ብዙዎች ዋልያዉ ነገ ከሚያደርገዉ ጨዋታ በፊት የወዳጅነት ጨዋታ አለማድረጉ እንደሚጎዳዉ ይናገራሉ፤ነገር ግን ዋልያዉ እስካሁን ካሸነፈባቸዉ ጨዋታዎች ምንም አይነት ድክመት ለማሻሻል ሳይችል ሌላ ጨዋታ ማድረግ ትርጉም አልባነቱ ይጎላል፤ አርቆ ማሰብ በዋልያዉ አከባቢ መኖሩ እጅግ አስፈላጊ ነዉ፤ናይጄሪያን ማሸነፍ ይቻላል፤አለም ላይ ያለን ጠንካራ ቡድንንም እንዲሁ…ነገር ግን ምንም ጥንካሬ ሳይኖር ትልቁን ሆነ ትንሹን ቡድን ማሸነፍ ዋጋቢስ ነዉ፤ከዚህ በፊት የነበሩት ድንገቴ ቡድኖች እንዳመጡት የሚረሳ ዉጤት ከመመስከር በስተቀር!!
ናይጄሪያ…የኋላን ማስተዋል….
ስለ ናይጄሪያ ጨዋታ ሲነሳ ሰዎች የኋላን ማየት አስፈላጊ አለመሆኑን ሲናገሩ ነበር፤ምክንያቱም ናይጄሪያ ምን ያህል በሽንፈት እንዳቆሰለን ስለሚታወቅ…ነገሩ ግን ህልም ተፈርቶ….እንደሚባለዉ ነዉ፤ናይጄሪያ በልጦ እስከዛሬ አሸንፎናል፤ይህ ሀቅ ነዉ..ዛሬም ቢወራ ከታሪክነት ባለፈ ለምን እንደበለጠን መማሪያ ይሆናል፤ትላንት የበለጠበትን መንገድ የያኔ ተጫዋቾች (አሁን በአሰልጣኝነት እና ዙሪያዉ ያሉ) በሚገባ አስረድተዉ አሁን ዋልያዉ እንዴት መብለጥና ማሸነፍ እንዳለብን ማስረዳት ይችላሉ፤አለበለዚያ ግን የኋላን ትቶ አልያም ማንሳቱን ፈርቶ የአሁኑን ብቻ ማሰብ ጎዶሎነት ይሆናል፤ጸሀፊዉ ዳንኤል ክብረት እንዳስቀመጠዉ…. ’’ከታሪክ መማር የማይፈልግ ሰዉ ታሪካዊ ስህተትን ለመድገም የተረገመ ነዉ፤እንዲህ የሚያደርግ ግን እንስሳ ብቻ ነዉ፤እንስሳት ታሪክ የላቸዉም፤ታሪክ ስለሌላቸዉ የዛሬ 1ሺ አመት አንድ በሬ የሰራዉን ስህተት የዛሬዉ በሬ ይደግመዋል፤የዛሬ 3 አመት አንድ በግ የሰራዉን ስህተት ዛሬም ያዉ በግ ሊሰራዉ ይችላል፤የዛሬ 600 አመት ምድርን ስትጭር የነበረችዉ ዶሮ ዛሬም እንደምትጭረዉ ማለት ነዉ፤ዶሮዋ ለመጫር ነዉ እንጂ ለመብረር ልታስብ አትችልም፤ሰዉ ግን ከዚህ ዉጭ ነዉ፤ሰዉ ከትላንት ይማራል..ስህተቱን ያርማል……ስለዚህ የሰዉ ልጅ የትላንቱን ጥሩ ይዞ እንዲቀጥልና መጥፎዉን እንዲያርም የጎበጠዉን እንዲያቀና…ተብሎ የታሪክ ትምህርት የሚሰጠዉ..’’
ከስሜት ወደ እዉነት…
ኢትዮጲያ እንድታሸንፍ የማይፈልግ የለም፤አስተማማኝ ቡድን ቢኖራት ምን ግዜም የምትታወቅበት ጥንካሬ ብታሳይ የሁሉም ምኞት ነዉ፤ነገር ግን ነገ በማይደገም አካሄድ ቡድንዋ በዉጤት ሲደለል ዝም ማለትም ተገቢ አይሆንም፤ዉጤት ያመጡ ሰዎች ክብር ይገባቸዋል፤ሽልማትም ቢጎርፍላቸዉ አስፈላጊ እና የሚበረታታ ነዉ፤ነገር ግን ዉጤት ያመጡበትን መንገድ መመርመር ደግሞ እዉቅና ከመስጠት የተለየ እይታን ይጠይቃል፤ጥሩ ያልሆነን ቡድን እላይ ሰቅሎ ሲፈጠፈጥ ከመሳቀቅ ከመነሻዉ እያሸነፈም ቢሆን በድፍረት ስህተቱን መጠቆም አስፈላጊ ነዉ፤ የባለፈዉ ሳምንት ጨዋታንም በዚህ መነጽር መቃኘቱ ጠቃሚ ነዉ፤የመጀመሪያዉ ነገር ከጨዋታዉ በፊት ይነገሩ የነበሩ የሁለቱ በድኖች ልዩነቶች አሁንም እንዳሉ ተረጋግጥዋል፤ናይጄሪያ በኬሺ የተጫዋችነት ዘመን የመንግስቱ ወርቁን ቡድን በአካል ብቃት ጥንካሬ እንደበለጡት ዛሬም የሰዉነትን ቡደን ከ30 አመታት በሁዋላም በልጠዋል፤ይህን ነገር ከእኔ ከጻሀፊዉ..ከናንተ አንባቢዎቸ እና ከአሰልጣኞች በላይ ተጫዋቾቹ ያቁታል፤ሁሌም በተደጋጋሚ ይናገሩታል፤ለዚህም ይመስላል ያለወትሮዉ በግምት ይላኩ የነበሩ ኳሶች የቀነሱት…ተጫዋቾቹ ኳስዋን በሚችሉት መንገድ በመሬት በአጭር ቅብብል ለመብለጥ ጥረዋል፤ከሌላዉ ጊዜ በተለየም ከተከላካዮቹ ደፍሮ የሚቀበል አማካይ ብቅ ብልዋል፤እሱም አዳነ ግርማ ነዉ፤የዋልያዎቹን ልምምድ ላለፉት 2ት አመታት በቅርበት ስከታተል የኳስ ብልጫን ለመዉሰድ የሚያስቸል ልዩ ስልጠና አላየሁም፤እናም አዳነ እና ጓደኞቹ ያደርጉ የነበሩት እንቅስቃሴ በትሬኒንግ የተነደፈ ስላለመሆኑ የቅብብላቸዉ መጨረሻ ያሳብቃል፤ለ6ት በራሳቸዉ ሜዳ ይቀባበላሉ..ከዛም በግምት ኳሶች ይጣሉና አጥቂዎቹ አላስፈላጊ ድካም ዉስጥ ይገባሉ፤ያም ቢሆን ግን ናይጄሪያን በፈለገዉ መጠን እንዳይንቀሳቀስ አድርገዋል፤የዚህ ነገር መነሻ የሆነዉ ተጫዋች በጊዜ ከተቀየረ ደግሞ ከርሞም ይህ አይነቱ አጨዋወት ተፈላጊ አለመሆኑን ያሳያል፤አሰልጣኝ ሰዉነት ከጨዋተዉ በሁዋላ ከአንድ ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ..”አሁን ጊዜዉ የመጫወት ነዉ፤ተጫዉቶ ማሸነፍ ያስፈልጋል፤ይህንንም ለመተግበር ሞክረናል” የሚል አንደምታ ያለዉ አስተያየት ሰጥተዋል ፤የመጀመሪያዉ ነገር መጫወት ከተፈለገ..እናም በመጫወት ብልጫ መዉስድ እንደሚቻል ከተረጋገጠ መጫወት የሚችሉ ተጫዋቾችን ለምን አልተካተቱም ?ይሆናል ጥያቄዉ…….ለማስረጃ ያህል መሀል ክፍሉን ለ90 ደቂቃ ተፈራርቀዉ ከተጫወቱት አስራት..አዳነ..አዲስ..እና ምንያህል ..ዉስጥ አንዳቸዉም በክለባቸዉ የጨዋታ አቀጣጣይነት ሚና ኑርዋቸዉ አያቅም፤አዳነ አጥቂ..አስራት እና አዲስ ቀሚ..ምንያህል የክንፍ ተጫዋቾች ናቸዉ፤እናም የመሀል ክፍል ብልጫ ያለመሀል ተጫዋች..ለዚያዉም የመፍጠር ብቃቱ ደካማ የሆነን ይዞ ማሰብ ከባድ ይሆናል፤ሀገሪቱ ደግሞ የአማካይ ተጫዋች ደሀ አይደለችም..ሌላዉን እንተወዉና የአዲስ አበባ ስታድየም መጫወቻ ሜዳ ሁሌም የመሀል ክፍሉ ሳር በቶሎ መበላት ለዚህ የማይናገር ምስክር ነዉ!!! ናይጄሪያ ጋር እንዴት መጫወት እንዳለብ እና እንዴት መጫወት እንደሌለብን በጨዋታዉ ታይትዋል፤የዚህ ቀን ችግር ግን የተጀመረዉ ዋልያዉ አሸናፊ ሆኖ ከማንም በላይ በተባለባቸዉ የቦትስዋና..ሴንትራል አፍሪካ..ደቡብ አፍሪካ ጨዋታዎችም ጭምርም ነበር፤በነዚህ ጨዋታዎች በየደቂቃዉ የሚጠልዝ..ኳስ ከእግሬ ዉጭልኝ በሚል መንፈስ የሚጫወት ቡድን ነበር፤ያም ቢሆን ግን ስላሸነፈ ከነስህተቱ ተንቆለጳጰሰ፤ድል ማድረግ እናም መመስገን በጣሙን ጥሩ ነገር ነዉ፤ነገር ግን ምንም ላይ ያልተመሰረተ ድል ነገ ምንም ላይ ሲጥል የናይጄሪያ አይነት ዱብ እዳ ያስከትላል፤
መፍትሄ…
ችግር የመፍትሄ ቁልፍ ነዉ፤እናም ኢትዮጵያ እግር ኳሴ አድግዋል ባለችበትም ሆነ በደከመችበት ጊዜ ያለመታከት የሚያሸነፍኑን የምእራብና ሰሜን አፍሪካ ቡድኖችን ለመብለጥ ወደ እዉነታዉ መምጣት አለብን፤”እኔ ጢቅ ጢቅ ጨዋታ የሚጫወት አልፈልግም.የሚጋጭ የሚፋለጥ እንጂ” የሚል አስተሳብ ያለዉ አሰልጣኝ ናይጄሪያም ሲመጣ ተጋጥቶና ተፋልጦ አሸንፎ ማሳየት ይኖርበታል፤አልያም ደግሞ አስቀድሞ በኳስ መብለጥ አለብን የሚለዉን መያዥ ይኖርበታል፤እኔ ይህንን የምጽፈዉ ላለፈዉ ቡድን አይደለም፤ከዚህ በኋላ ለሚመጣዉ ነዉ፤እንኳን አሰልጣኙና ባለሙያዉ ቀርቶ ተመልካቹ እንኳን ለይቶ ኳስ የሚጫወቱ የዉጭ ቡድኖችን የነፍሱ ያህል በሚወድበት ሀገር ለጥለዛ ና አካል ግዝፈት የሚሰጠዉ ትኩረት መቅረት አለበት፤እከሌ ምን ያህል ኳሶችን አጨናገፈ ሳይሆና እከሌ ምን ያህል ኳሶችን አስተካክሎ ሠጠ መመዘኛ መሆን አለበት፤፤ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ክህሎት ያልዋቸዉ ተጫዋቾች ሀገር መሆንዋ ለክርክር ማቅረብ ጉንጭ ማልፋት ነዉ፤አለምም በዚህ በዉብ እግር ኳስ ቅኝት እየተመራ መሆኑ ለእግር ኳሱ ትልቅ እድል ነዉ፤አለም ተጫዉቶ ስለማሸነፍ እያዜመ ነዉ፤ጀርመን ከጉልበት ወደ ጥበብ መንገዱን ጠርግዋል፤ስፔን እግር ኳሱን በአጭር ቅብብል መደብ አናቱ ላይ ከወጣች ቆይታለች፤ዋልያዉስ???አፍሪካን ለመቆጣጠር ጊዜዉ አሁን ነዉ!!ከፍለጠዉ ቁረጠዉ አጨዋወት ወደ ጭንቅላት ጨዋታ መቀየር..ለዚህ ደሞ በቂ ተጫዋቾች በኢትዮጲያ ይገኛሉ፤እናም ለዋልያዉ ትንሳኤ በመልሱ የካላባር ጨዋታ ሆነ በቀጣየቹ ዉድድሮች ይህንን መሞከሩ በእዉር ድንብር ከመሄድ በእዉቀት አለምን መከተልን ያስገኝለታል!!!!

Mar 22, 2012

በሊባኖስ በሞተችው ኢትዮጵያዊት አሠሪ ላይ ክስ ተመሠረተ

ራሷን አጠፋች በመባሉ ላይ ጥርጣሬ አለን›› በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት

በሊባኖሳዊ አሠሪዋ መሬት ለመሬት ስትጎተት፣ ስትንገላታና ስትደበደብ በሊባኖሱ ኤልቢሲ ቴሌቪዥን ጣቢያ የታየችው ኢትዮጵያዊቷ ዓለም ደቻሳ ደሲሳ ራሷን እንዳጠፋች በመገለጹ፣ ራሷን በመግደሏ ላይ ጥርጣሬ አለን የሚለው በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በአሠሪዋ ላይ ክስ በመመሥረት የአሟሟቷ ሁኔታ እንዲጣራለት ጠይቋል፡፡
ከዚህ በፊት በሠራተኞቻቸው ላይ በደል የፈጸሙ አሠሪዎች የተቀጡት የ15 ቀናትና የአንድ ወር እስር ብቻ ነው፡፡

በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ኃላፊ አቶ አሳምነው ደበሌ ቦንሳ በስልክ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2004 ዓ.ም. እሳቸውን ጨምሮ ሌሎችም የተኛችበት ሳይኪያትሪክ ዲ.ላ. ክሮክሲ ሆስፒታል ድረስ በመሄድ ጠይቀዋታል፡፡ ሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ደግሞ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሄደው አይተዋት ሰላም መሆኗንና የአዕምሮዋ ሁኔታ የተረጋጋ እንደነበረ ነግረዋቸዋል፡፡ ረቡዕ መጋቢት 5 ቀን 2004 ዓ.ም. አሠሪዋ የፈጸመባትን በደል በተመለከተ ጉዳዩን ከያዘው ፖሊስ ጋር ስለክሱ ለመነጋገር ሲሄዱ፣ ፖሊሱ ‹‹ልጇቷ እኮ ሕይወቷ አልፏል!›› በማለቱ ወዲያው ወደ አዕምሮ ሕክምና ሆስፒታሉ ሄደው፣ ሕይወቷ ማለፉን ከሕክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል፡፡

‹‹የሆስፒታሉን አስተዳደርና ሕክምና የሚያደርጉላትን ዶክተር አነጋገርናቸው የሆነው ምንድነው? ከዚህ ቀደም በሆስፒታሉ የገቡ ኢትዮጵያውያን ታክመው ድነው ወጥተዋል፡፡ በቅርብ ቀን ሆስፒታል የገባችው ዓለም ደቻሳ ደግሞ ሞታለች ተብሏል ብለን ጠየቅን፤›› የሚሉት አቶ አሳምነው፣ ከሕክምና ባለሙያዎቹ ያገኙት መልስ፣ ‹‹በመልካም ሁኔታ ላይ ስለሆንሽ ከሆስፒታል ወጥተሽ አገርሽ እንድትመለሽ ይደረጋል ብለን ነግረናት ነበር፡፡ በጥሩ ሁኔታ ላይም ነበረች፡፡ ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ የምትከታተላት ነርስ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተኝታ አይታታለች፡፡ 11 ሰዓት ላይም ተኝታ ነበር፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በ12 ሰዓት ስትጎበኛት ለአየር ማስገቢያ በተከፈተ ኮሪደር ላይ አንሶላ ቀዳ ራሷን አጥፍታ ተገኘች፤› የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

አስከሬኗን አይተው ባያረጋግጡም ስለ መሞቷ እርግጠኛ መሆናቸውንም እንደነገሯቸው አቶ አሳምነው ገልጸዋል፡፡ ራሷን ማጥፋትና አለማጥፋቷን በሚመለከት የአሟሟቷ ሁኔታ ላይ ጥርጣሬ ስላላቸው ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀው ውጤቱን እየተጠባበቁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ‹‹የሰማነው ረቡዕ መጋቢት 5 ቀን 2004 ዓ.ም. በአምስት ሰዓት ላይ ሲሆን፣ የሞተችው ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ነው፤›› የሚሉት አቶ አሳምነው፣ ክስ መመሥረታቸውን ተናግረዋል፡፡ በአሟሟቷ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ሲገልጹም፣ ‹‹ሌሎች በሆስፒታሉ የሚታከሙ ሁለት ኢትዮጵያውያን አሉን፡፡ በሌላ በኩል የአዕምሮ ሕክምና የሚሰጥ ሆስፒታል ውስጥ ታካሚ ራሱን እስኪያጠፋ ዕድል የሚሰጥ አሠራር የሌለና ጥበቃውም የተጠናከረ ነው፡፡ ጥንቃቄና ክትትል ያለበት ስለሆነ እንዴት ራሷን ልታጠፋ ቻለች የሚለውን እንዲጣራ እያደረግን ነው፤›› ብለዋል፡፡

የአዕምሮ ችግር አለባት የተባለውን ማረጋገጣቸውን በተመለከተም በሕክምና ችግሩ አለባት ተብሎ ሆስፒታል መግባቷን ተናግረዋል፡፡ ዓለምን ጠይቀዋት እንደተረዱትም፣ ሊባኖስ የገባችው ከሁለት ወራት በፊት ነው፡፡ አገባቧ በሕገወጥ መንገድ ቢሆንም በሕገወጥ መንገድ እንደገባች አታውቅም፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ሊባኖስ ለቤት ሠራተኝነት የሚደረገውን የሥራ ጉዞ እንዳገደችም መረጃው የላትም፡፡ በመሆኑም ሊባኖስ የገባችው ከሰው ገንዘብ ተበድራ ሲሆን፣ ዓላማዋ ደግሞ ሠርታ ብድሯን ለመክፈልና ልጆቿን ለማሳደግ ነበር፡፡ ሊባኖስ የገባችው በሕገወጥ መንገድ መሆኑን ስትገነዘብ ግን አዕምሮዋ ተነካ፡፡ ተበሳጨች፡፡ ሆኖም ያለባት ጭንቀት እንጂ ሙሉ ለሙሉ የአዕምሮ ህመም አልነበረም ብለዋል፡፡

የ33 ዓመቷ ዓለም ደቻሳ ደሲሳ የቡራዩ ከተማ ነዋሪ እንደሆነች፣ ከባሏ መፋታትዋንና በዚህም ብስጭት እንዳለባት ሆስፒታል ሆና በጎበኟት ወቅት እንደነገረቻቸው አስረድተዋል፡፡ በእነሱ በኩልም መጀመርያ ጤንነት እንደሚቀድም፣ በማስከተል ደግሞ ገንዘቡን ልታገኝ እንደምትችል አሳምነዋት ደህና ሆና እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በርካታ ኢትዮጵያውያት ብዙ በደሎች ይፈጸሙባቸዋል፤ በዓለም ላይ የድብደባና የማንገላታቱ ጥቃት የተፈጸመው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ፊት ለፊት ነው፤ እናንተ አላያችሁም ነበር ወይ? በማለት ለአቶ አሳምነው ጥያቄ አንስተን ነበር፡፡ በቆንስላነት ከተሾሙ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠሩት አቶ አሳምነው እንደሚሉት፣ ከጅምሩ አንሥቶ ኢትዮጵያውያት በሕገወጥ መንገድ እንዳይመጡ እያስተማሩና እየረዷቸው ነው፡፡ በሕገወጥ መንገድ የሚመጡትና ችግር ውስጥ የተዘፈቁትም ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ በየቦታው መደፈርን ጨምሮ በርካታ በደሎች አሉ፡፡ የዓለም ጉዳይ ይፋ የወጣው በአጋጣሚ ሚዲያ ስላገኘው ነው፡፡ የዓለምን ጉዳይ በተመለከተም አሠሪዋ ቆንስላው ጽሕፈት ቤት አምጥቷት አገሬ እሄዳለሁ እያለችው እንደሆነ ሲነግራቸው መብቷ ነው ብለው መመለሳቸውን፣ ከዚያም ራሴንም አጠፋለሁ እያለች ነው በማለቱ እንደዚህ ከሆነ የማሳከም ግዴታ ስላለብህ ሆስፒታል ውሰዳት ብለውት ተስማምተው ከጽሕፈት ቤቱ ከወጡ በኋላ ውጭ ሲደርሱ መኪና ውስጥ ግቢ አትግቢ በሚል እንግልት፣ ድብደባና ጉተታ በዓለም ላይ መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡

አቶ አሳምነው እንደሚሉት፣ ግብግቡ ሲፈጠር ከጽሕፈት ቤታቸው ወጥተው ልጅቷን አስጥለዋል፡፡ ፖሊስ ጠርተውም አሠሪዋ  በቁጥጥር ሥር እንዲውል፣ እሷም ሆስፒታል እንድትሄድ አስደርገዋል፡፡ ሆኖም የፖሊሱም ሆነ የእሳቸው ተሳትፎ ሳይካተት ልጅቷ ስትደባደብና በግዳጅ መኪና ውስጥ ስትገባ ያለው ምስል ብቻ በሚዲያ ተለቋል፡፡

በቆንስላው በኩል የአቅማቸውን ያህል እየሠሩ መሆኑን፣ ከዚህ ቀደም 300 ሰዎች ምሕረት ተደርጎላቸው ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሱ በመግለጽ፣ የቆንስላ ጽሕፈት ቤቱ ለዜጎቹ ትኩረት እንዳልሰጠ ተደርጎ የሚፈረጀው ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ በጽሕፈት ቤቱ በኩል ዜጎችን ከገቡበት ችግር ለማውጣት እየተሠራ መሆኑንና  በሥራቸው በብዛት የተጠመዱትም ኢትዮጵያውያኑ ሲቸገሩ በመርዳት፣ አገራቸው እንዲመለሱ በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በቅርብ ቀን ከሐዲያ የመጣችና ከሐዲያ ቋንቋ በስተቀር መግባባት የማትችል ልጅ ማግኘታቸውን፣ በአስተርጓሚ በኩል እንደተረዱት ልጅቷ ደቡብ አፍሪካ እንዳለች የምታውቅ መሆኗን የሚገልጹት አቶ አሳምነው፣ የአዕምሮ ጭንቀት ስለነበረባት ሆስፒታል እንድትገባ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ ከሐውዜን (ትግራይ) የመጣችም እንዲሁ የቋንቋው ተናጋሪ ፈልገው እንዳነጋገሯትና በአጠቃላይም በሊባኖስ ያለው ችግር በጣም አስከፊ ገጽታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህንን ለማቃለል ዜጎች በሕጋዊ መንገድ እንዲገቡ፣ ዕድሜያቸውና የትምህርታቸው ሁኔታ ተጠንቶ በሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ብቻ ሕጋዊ ሆነው የሚመጡበትን ፕሮፖዛል አቅርበውም እንዳልተቀበሏቸው ገልጸዋል፡፡

እገዳው ቢኖርም ኢትዮጵያውያኑ ሕገወጥ ሆነው ወደ ሊባኖስ መግባታቸው ስላልቀረ፣ በኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጋ የሥራ ዕድል መፍጠር እስከሚቻል ድረስ በሕጋዊ መንገድ የሚመጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ መሠረት፣ በቤይሩት በአጠቃላይ ሕጋዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊ የቤት ሠራተኞች የሉም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎችን መብት የሚያስጠብቅ የጋራ የሥራ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ኢትዮጵያውያን ወደ ቤይሩት እንዳይሄዱ እገዳ ከጣለ ከሦስት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ቀደም ባሉት ጊዜያት በየመን በኩል አሁን ደግሞ በሱዳን ወደ ቤይሩት የሚጓዙ ሴቶች ቁጥር በጣም ጨምሯል፡፡

እገዳው ከመጣሉ በፊት ሕጋዊ ሆነው ወደ ቤይሩት የገቡ ኢትዮጵያውያን ጊዜያቸውን ሲጨርሱ ወደ አገራቸው መመለስ ሲገባቸው ባለመመለሳቸው ሕገወጥ ሆነዋል፡፡ ኢትዮጵያ ዜጓቿ ወደ ሊባኖስ እንዳይሄዱ እገዳ ከጣለች ወዲህ የሄዱት በሙሉ ደግሞ በሕገወጥ መንገድ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ጋር የዜጎችን መብትና ጥቅም የሚያስጠብቅ የጋራ የሥራ ስምምነት ተፈራርማ የምትገኝ አገር ኩዌት ብቻ ናት፡፡ የሳዑዲ ዓረቢያ ደግሞ በሒደት ላይ ይገኛል፡፡ በሊባኖስ ከ60 እስከ 70 ሺሕ የሚደርሱ ኢትዮጱውያን ይኖራሉ ተብሎ እንደሚገመት አቶ አሳምነው ገልጸዋል፡፡

መንግሥት በዋልድባ ገዳም የስኳር ልማት አላካሄድኩም አለ

ዳሙን በከበበው ዛሬማ ወንዝ ላይ ልማት እየተካሄደ ነው

በጥንታዊውና በአገሪቱ ካሉ ቅዱሳን መካናት በቀደምትነቱ የሚታወቀው የዋልድባ ገዳም ውስጥ ምንም ዓይነት የስኳር ልማት ፕሮጀክት አለማካሄዱንና የማካሄድ ዕቅድ እንደሌለው ያስተባበለው የኢትዮጵያ የስኳር ልማት ኮርፖሬሽን፣ በበርካታ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችም ሆነ በገዳሙ መነኮሳት የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ያጣጣለው ‹‹ሌላ አጀንዳ ባላቸው ሰዎች የተነሳ ጥያቄ ነው፤›› በማለት ነው፡፡ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ ከሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በወልቃይት፣ በአክሱምና በመቀሌ ያደረጉትን ስብሰባ አጠናቀው ትናንት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ በገዳሙ የቀረበውን ተቃውሞ አግባብ ባለው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር መሠረት ያልቀረበ፣ ይልቁንም የገዳሙ አንዳንድ መነኮሳት ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ያሰሙት አቤቱታ ትርጉም የሌለውና ተገቢ ያልሆነ በማለት ኮርፖሬሽኑ አጣጥሎታል፡፡

ነገር ግን የኮርፖሬሽኑ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የዋልድባን ገዳም ከከበቡት ወንዞች አንዱ በሆነው የዛሬማ ወንዝ ላይ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኘው ወልቃይት ወረዳ ላይ የሚካሄደው የስኳር ፕሮጀክት 25 ሺሕ ሔክታር መሬት የሸንኮራ አገዳ የሚለማበት ሲሆን፣ በቀን 10 ሺሕ ቶን አገዳ የሚፈጭ ፋብሪካ የሚገነባበት ነው፡፡

ፕሮጀክቱ የሚካሄድባቸው ቦታዎች ዛሬማ፣ ዱቁቆና ተከዜ ሸለቆ ሲሆኑ በተለይ የዛሬማ ወንዝ ለገዳሙ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ቢሆንም፣ ሪፖርተር ከኮርፖሬሽኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘው መረጃ ግን ያንን የሚያስተባብል ነው፡፡

ወንዙን በመገደብ 3.8 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ በመያዝ ለአገዳ ልማት እንደሚጠቀምበት ያስታወቀው ኮርፖሬሽኑ፣ ከስኳር ፋብሪካው በዓመት 284 ሺሕ ቶን ስኳር እንዲሁም 26.8 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል ለማምረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ከዚህም ባሻገር በአካባቢው 3,442 መኖርያ ቤቶች እንዲሁም 120 የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እንደሚገነቡ ሲጠበቅ፣ ሥራውን የሚያካሂድበትን ጽሕፈት ቤት በማይገባ ከተማ እንደከፈተ ታውቋል፡፡ እስካሁንም የግድብ ግንባታው ቁፋሮና እርሻውን፣ ፋብሪካውንና የመኖርያ መንደሮችን የሚያገናኙ መንገዶችም እተገነቡ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በትናንትናው የዜና እወጃ ምሽት ላይ ስቱዲዮ ተገኝተው በገዳሙ ላይ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ በገዳሙና በስኳር ፕሮጀክቱ መካከል የስድስት ሰዓት ያህል ርቀት የሚገኝ ከመሆኑም በላይ በቅዱስነቱ ሳይነካ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ሆኖም ግን በታህሳስ ወር ላይ ገዳሙ በስኳር ፕሮጀክት ግንባታ ሳቢያ እየታረሰ፣ የቅዱሳን አባቶች አጽም እየፈለሰ፣ መቃብራቸው እየተደፈረና የጥርጊያ መንገድ እየወጣበት እንዲሁም ደግሞ ለፓርክነት እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ከገዳሙ ውስጥ ከሚገኙ ልዩ ልዩ ገዳማት መፍትሔ እንዲሰጧቸው  በጹሑፍ መጠየቃቸው የሚታወስ ቢሆንም፣ አቶ ዓባይ ግን በመነኮሳቱ ያልቀረበ ጥያቄ በማለት ውድቅ ከማደረጋቸውም በላይ፣ ለገዳሙና ለሃይማኖት በመቆርቆር ሳይሆን በሰበቡ ተጠቅመው ተቃውሞ ለማስነሳት የፈለጉ ሰዎች ያነሱት ጥያቄ ነው ብለውታል፡፡

ጥያቄውን ያቀረቡት ግን የየገዳማቱ ተጠሪዎች እንደሆኑ ቢነገርም፣ የቤተ ክህነት አጣሪ ኮሚቴ በቦታው ተገኝቶ ማጣራቱንና ምንም ዓይነት ጉዳት በገዳሙ ላይ አይደርስም ማለቱ  ተነግሯል፡፡ ያም ሆኖ አቶ ዓባይ የሰዎች አጽም በክብር እየተነሳ እንደሚገኝ፣ በፕሮጀክቱ አካባቢ ተነሺ ለሆኑ ሰዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲዛወሩ ከሕዝብ ጋር ውይይት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

የዋጋ ግሽበት የአገሪቱ ፈታኝ ችግር መሆኑን መንግሥት አመነ

መንግሥት ለዘይት ግዥ 1.5 ቢሊዮን ብር ገደማ ይደጉማል

ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የተከሰተው የዋጋ ግሽበት በአገር ደረጃ፣ በመንግሥት፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ደረጃ ፈታኝ ችግር መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ በአገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ግሽበት ተከትሎ መንግሥት የዋጋ ንረት የታየባቸውን መሠረታዊ ፍጆታዎች ከውጭ በማስመጣት በድጐማ ለኅብረተሰቡ ቢያቀርብም፣ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈለገው ለውጥ ሊመጣ አለመቻሉን የጠቆሙት ሚኒስትሩ አቶ ሱፍያን አህመድ፣ አገሪቱ የገጠማትን ይህንን ፈታኝ ችግር ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ ከሁሉም በላይ በዋጋ ግሽበቱ የሚጐዳው ዝቅተኛው የኅብረተሰብ ክፍሉ በመሆኑ፣ ችግሩ በአገር ደረጃ የሚካሄደውን ድህነትን የመዋጋት እንቅስቃሴ የሚፈታተን ሆኗል፡፡ መንግሥት በአገራቱ ውስጥ እጥረት የሚታይባቸው ሦስት መሠረታዊ የምርት ፍጆታዎች (ስንዴ፣ ዘይትና ስኳር) ከውጭ አገር በመግዛት በአገር ውስጥ ማከፋፈል ከጀመረ የቆየ ቢሆንም፣ ችግሩ እየተባባሰ ከመሄድ ውጪ የመጣ ለውጥ የለም ብለዋል፡፡

የመሥርያ ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ትናንት ለተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት አቶ ሱፍያን እንደገለጹት፣ መንግሥት ከውጪ ያስመጣቸው ምርቶች በጣም ቀልጣፋ የሆነ ግልጽነት የተላበሰ የግብይት ሥርዓት ተዘርግቶ ለኅብረተሰቡ ቢሰራጩ ኖሮ የዋጋ ግሽበቱ በከፍተኛ ደረጃ ሊቀነስ ይችል ነበር፡፡

የዋጋ ግሽበቱን ይቀንሳል በሚል እምነት ባለፈው ዓመት ብቻ መንግሥት ሦስት ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ፣ 240 ሚሊዮን ሊትር ዘይትና 1.2 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ከውጭ ገዝቷል፡፡ በያዝነው ዓመት ደግሞ አምስት ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ፣ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የተገዛ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ እየተከናወነ ያለው የ300 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ግዥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጓጉዞ አገር ውስጥ የሚገባ መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዓመት 30 ሚሊዮን ኩንታል ገደማ ስንዴ እንደምታመርት የጠቆሙት አቶ ሱፍያን፣ መንግሥት ከወጪ ያስመጣው ስንዴ ታክሎበት በትክክል ለተጠቃሚው ኅብረተሰብ ቢሰራጭ የዋጋ ግሽበቱ ሊከሰት እንደማይችል ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት በዓለም ገበያ ከ30 እስከ 35 ዶላር የሚሸጠው አንድ ኩንታል ስንዴ ኢትዮጵያ ውስጥ ለኅብረተሰቡ በ520 ብር፣ ለዱቄት ፋብሪካዎች ደግሞ በ560 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት በድጐማ ገዝቶ ያስገባው ስንዴ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በዋና ዋና ከተሞችና በክልል ከተሞች መስተዳድር ጭምር የሚከፋፈል መሆኑን አቶ ሱፍያን አስረድተዋል፡፡ በአገሪቱ ከሚመረተው ስንዴ 70 በመቶ ያህሉ ለዱቄት ፋብሪካዎች ጥቅም የሚውል መሆኑን ጥናቶችን ጠቅሰው የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ ቁጥራቸውና የመፍጨት አቅማቸው የሚታወቀው የዱቄት ፋብሪካዎች ስንዴ እንዲያገኙና የፈጩትንም ስንዴ ለዳቦ ቤቶች የሚያቀርቡበት ሁኔታ መመቻቸቱን አስረድተዋል፡፡ ክልሎችም ራሳቸው በመረጧቸው አከፋፋዮች አማካይነት በወረዳና በዞን ከተሞች ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚያከፋፍሉበት ዕድል መፈጠሩን አክለው ገልጸዋል፡፡ የዘይት ግዥን በተመለከተም አንድ ሊትር ዘይት ከውጭ ገዝቶ አገር ውስጥ ለማስገባት 30 ብር የሚፈጅ መሆኑን፣ ለእያንዳንዱ ሊትር ዘይትም መንግሥት ከአራት እስከ ስድስት ብር ድጐማ እንደሚያደርግ አቶ ሱፍያን ገልጸዋል፡፡ ይህንን የሚኒስትሩ መረጃ ሲሰላ በያዝነው ዓመት ብቻ ለሚከናወነው የ300 ሚሊዮን ሊትር ግዢ የምግብ ዘይት መንግሥት 1.5 ቢሊዮን ብር ይደጉማል ማለት ነው፡፡

የስኳር ምርት እጥረትም ቢሆን አሁንም ድረስ መፍትሔ የተገኘለት አይመስልም፡፡ ከሦስት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ የራሷን ፍላጐት ከመሸፈን አልፋ በዓመት ከ100 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ኩንታል ስኳር ወደ ውጭ ትልክ እንደነበር ያስታውሱት አቶ ሱፍያን፣ ከሦስት ዓመታት ወዲህ ግን የስኳር ፍጆታ በመጨመሩ መንግሥት በዓመት እስከ አንድ ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ ስኳር ከውጭ አገር ገዝቶ ለማስገባት መገደዱን ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ዓመት 1.2 ሚሊዮን ኩንታል ዘንድሮ ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ኩንታል ስኳር መግዛቱንም አክለው ገልጸዋል፡፡ አሁን ባለው ዓለም አቀፍ ገበያ አንድ ኩንታል ስኳር ገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ሁለት ሺሕ ብር ይፈጃል፡፡ በአገር ውስጥ የሚሸጥበት ዋጋ ግን 1400 ብር መሆኑን አቶ ሱፍያን ይገልጻሉ፡፡ 

በአገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ግሽበት ለመቀነስ መንግሥት የፍጆታ ምርቶችን ከውጭ እየገዛ በድጐማ ለኅብረተሰቡ የሚያከፋፍለው እስከ መቼ ድረስ ነው? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት በመሥራት የግብይት ሥርዓቱን ዘመናዊ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ሱፍያን፣ ከዋጋ ግሽበት ጋር በተያያዘ የውጪ ኩባንያዎች ሚና ምን ሊሆን ይችላል? በሚለው ጉዳይ ላይ ጥናት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ እርሳቸው እንዳሉት፣ በተለይም በጅምላ ንግድ ደረጃ የኢትዮጵያ ገበያ ለውጭ ኩባንያዎች ክፍት ቢሆን የሚያስገኘው ጥቅምና የሚያስከትለው ስጋት ምንድነው? የሚለውን ጉዳይ ለማጥናት በሚመለከታቸው መሥርያ ቤቶች ሚኒስትሮች የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የተለያዩ አገሮች ልምድ ታይቷል፡፡ ሚኒስትሩ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ዕድገትን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት እንደተጠቀሰው በበጀት ዓመቱ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት 11 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል፡፡ የኢንዱስትሪው ዘርፍም የ17.9 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

አቶ ሱፍያን ያቀረቡት የፌዴራል መንግሥት ፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት እንሚያሳየው፣ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ውስጥ ከታክስ ገቢ ብር 34,674.2 ሚሊዮን ብር፣ ታክስ ካልሆኑ ምንጮች ብር 8,578 ሚሊዮን ብርና በመሠረታዊ አገልግሎቶች ድጋፍና ዕዳ ቅነሳ ብር 1,944.6 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል፡፡ የውጭ ሀብት ግኝትና አስተዳደርን በተመለከተም በበጀት ዓመቱ ከውጪ ብድርና ዕርዳታ ወደ አገር ውስጥ ይፈሳል ተብሎ ከታቀደው 37.9 ቢሊዮን ብር ውስጥ በግማሽ ዓመቱ 20.4 ቢሊዮን ብር መገኘቱን የሚኒስትሩ ሪፖርት ያመለክታል፡