Oct 27, 2013

ኢትዬጲያ ቡና ከ ቲፒ ማዚምቤ በአዲስ አበባ…—600 ታዋቂ ሰዎች ይመጣሉ!


ሞ ኢብራሂም የተባለዉ ልጥጥ ሀብታም በየአመቱ የአፍሪካ ጥሩ ሰሪ መሪዎችን በመሸለም ይታወቃል፤ሞ ፋዉንዴሽን የተባለዉ የእርዳታ ድርጅቱ ከዚህ በፊት እንደ ማንዴላ እና መሰል መሪዎችን በመሸለም ይታወቃል፤ለምሳሌ አንዴ የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ መሪ ተብሎ የተመረጠ ሰዉ 5ሚልየን ዶላር ብር ስጦታ ከዛም በየአመቱ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ 200ሺ ዶላር ይበረክትለታል፤ዘንድሮ ከ48ት የአፍሪካ ሀገራት ለዚህ የሚመጥን ሰዉ አልተገኘም፤ነገር ግን ፕሮግራሙ ያለ ተመራጭ መሪ በሙዚቃ ሰዎች በእግር ኳስ ዉድድር ይካሄዳል፤600 ታዋቂ ሰዎች..መሪዎች እና የሙዚቃ ባለሙያዎች ይገኛሉ፤የሙዚቃ ዝግጅትም ይኖራል፤ገቢዉ ለባለሜዳዉ ቡድን ቡና ይሆናል፤
ይሄ ቱጃር ከ15ቀናት በሁዋላ በአዲስ አባ ስታድየም ኢትዮጲያ ቡና እና ቲፒ ማዚምቤን ያጫዉታል፤የአፍሪካ ህብረት መዲና ስለሆነች አዲስ አበባ ለዚህ ጨዋታ ቦታነት ስትታጭ ብዙ ደጋፊ ያለዉ ክለብ በሚል ኢትዮጲያ ቡና በዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ተመርጥዋል፤ዉድድሩ ጥቅምት 29 ይደረጋል፤ቲፒ ማዚምቤ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫን ወስድዋል፤ዘንድሮ ደግሞ በኮንፌዴሬሽኑ የፍጻሜ ተፋላሚ ነዉ፤
የሁለቱን ጨዋታ የሚመሩት ዳኞች ኢትዮያዉያን ናቸዉ፤በነገራችን ላይ ተፒ ማዚምቤዎች ኢትዮጲያዊዉን ዳኛ ዘካርያስን በሴካፋ ክለቦች ጨዋታ መተዉታል፤ሜዳዉ ዉስጥ ሮጦ አመለጣቸዉ እንጂ ብዙ ለካልቾና ለቡጢ የተዘጋጁ ተጫዋቾች ነበሩ፤ይህ የሆነዉ ከ2 አመት በፊት ነዉ፤የነሱ አሰልጣኝ የነበረዉ ዲዮጎ ጋርዚያቶ ነበር፤መቸስ ዘካርያስ እንዳያጫዉተን አይሉም….እሱስ ምን ያስብ ይሆን በሜዳዉ ሲያያቸዉ???

No comments: