May 17, 2012

ድምጽ አልባ ፊደላት

 ድምጽ አልባ ፊደላት

ፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮ
ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት
ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት
ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት
በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር
ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር
ይታየኛል ቃንቃ ይታየኛል ነገር
እዛም ከጨለማው ብቸኝነት ውጣት
ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችው ወጣት
ሂድና ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት
ምጋ በተፋችው በጭሶቹ መሃል
ሴትነት ሲበደል እህትነት ሲጣል
እናትነት ሲጎድል
ይታየኛል ቃንቃ ይታየኛል ፊደል።

ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን

1 comment:

Henok Sitotaw said...

ጸጋዬ ገ/መድህን “ድምጽ አልባ ፊደላት” ን አልገጠመም፡፡ ገጣሚው ኤፍሬም ስዩም ነው፤ ማስተካከያ ቢደረግበት መልካም ነው